የተርቲል አርማተርቲልቀጥታ ሬዲዮ

ሱራ አል ኢንሺቃቅ፦ ጽሑፉ እና የቁርኣን ፍቺ ትርጉሙ

በሙስሐፉ ውስጥ 84ኛው ሱራ ነው፤ 25 አንቀጾች አሉት፤ በገጽ 589 ይጀምራል።

ቲላዋዎቹን አዳምጥይህን ሱራ በሙስሐፉ ከተፍሲር ጋር አንብብ‹ ሱራ አል ሙጠፊፊንሱራ አል ቡሩጅ ›

بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

1. ሰማይ በተቀደደች (በተሰነጠቀች) ጊዜ፤

2. የጌታዋንም ትዕዛዝ በሰማች ጊዜ፤ (ልትሰማ) ተገባትም፤

3. ምድርም በተለጠጠች ጊዜ፤

4. በውስጧ ያለውንም ሁሉ በጣለችና ባዶ በሆነች ጊዜ፤

5. የጌታዋንም ትዕዛዝ በሰማች ጊዜ፤ (ልትሰማ) ተገባትም፤

6. አንተ ሰው ሆይ! አንተ ጌታህን (በሞት) እስከምትገናኝ ድረስ ልፋትን ለፊ ነህ። ተገናኚዉም ነህ።

7. ያ! መጽሐፉን በቀኝ እጁ የተሰጠውማ

8. በእርግጥ ቀላልን ምርመራ ይመረመራል።

9. ወደ ቤተሰቦቹም ተደሳች ሆኖ (በደስታ) ይመለሳል።

10. ያ ! መጽሐፉን በጀርባው በኩል የተሰጠው ግን

11. (ዋ! ጥፋቴ በማለት) ጥፋትን በእርግጥ ይጠራል።

12. የተጋጋመች እሳትንም ይገባል።

13. እርሱ በቤተሰቡ ውስጥ ተደሳች ነበርና፤

14. እርሱም (ወደ አላህ) ፈጽሞ እንደማይመለስ አሰበ።

15. አይደለም (ይመለሳል)፤ ጌታው በእርሱ (ሥራ) ተመልካች ነው።

16. ስለሆነም በወጋገኑ እምላለሁ።

17. በሌሊቱና በሰበሰበዉም ሁሉ፤

18. በጨረቃውም በሞላ ጊዜ (እምላለሁ)።

19. ከአንድ እርከን ወደ ሌላ እርከን በእርግጥ ትሸጋገራላችሁ።

20. የማያምኑት ለእነርሱ ምን አላቸው ( ምን ሆነው ነው)?

21. በእነርሱ ላይ ቁርኣን በተነበበ ጊዜ የማይሰግዱትስ ለእነርሱ ምን አላቸውና ነው?

22. ይልቁንም እነዚያ የካዱት ያስተባብላሉ።

23. አላህ በልቦቻቸው የሚቋጥሩትን ሁሉ አዋቂ ነው።

24. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአሳማሚ ቅጣት አብስራቸው።

25. እነዚያ በአላህ አምነው መልካም ተግባራትን የሰሩት ሲቀሩ፤ ለእነርሱማ የማይቋረጥ ምንዳ አላቸው።

የቁርኣን ፍቺ ትርጉም፦ Amharic Translation - Africa Academy፣ እትም 1.0.3፤ ከQuranEnc.com ያለ ምንም ለውጥ የቀረበ። (QuranEnc.com)

ትርጉም የቁርኣንን ፍቺዎች ያስተላልፋል እንጂ ራሱ ቁርኣን አይደለም፤ ቁርኣን ከላይ ያለው የዐረብኛ ጽሑፍ ነው።

ቲላዋዎቹን አዳምጥይህን ሱራ በሙስሐፉ ከተፍሲር ጋር አንብብ‹ ሱራ አል ሙጠፊፊንሱራ አል ቡሩጅ ›