በሙስሐፉ ውስጥ 91ኛው ሱራ ነው፤ 15 አንቀጾች አሉት፤ በገጽ 595 ይጀምራል።
بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
1. በጸሐይና በብርሀኗ፤ (እምላለሁ)
2. በጨረቃም ጸሐይን በተከተላት ጊዜ፤
3. በቀንም ጸሐይን በገለፃት ጊዜ፤
4. በሌሊቱም ጸሐይን በሸፈናት ጊዜ፤
5. በሰማይ እና በገነባትም፤
6. በምድር እና በዘረጋትም፤
7. በነፍስም ባስተካከላትም
8. አመጽዋንና ፍርሃቷንም ባሳወቃት (አምላክም እምላለሁ)።
9. (ነፍስን) ከኃጢአት ያጠራ ሰው ሁሉ በእርግጥ ተሳካለት።
10. በኃጢአትም የሸፈናት ሰው ሁሉ በእውነት አፈረ (ከሰረ)።
11. ሰሙድ ወሰን በማለፍዋ ምክንያት አስተባበለች፤
12. እጅግ መናጢዋ በተነሳ ጊዜ።
13. ለእነርሱም የአላህ መልዕክተኛ (ሷሊህ)፡-የአላህን ግመልና የመጠጥ ተራዋን (ጠብቁላት) አላቸው።
14. እነርሱ አስተባበሉትም፤ ከዚያ ወጓት፤ በኃጢአታቸዉም ምክንያት ጌታቸው (ቅጣትን) በእነርሱ ላይ ደመደመባቸው (ደመሰሳቸው)፤ አስተካከላትም።
15. ፍፃሜዋንም አይፈራም። (አላህም የዚህን ቅጣት ፍፃሜ አይፈራም።)
የቁርኣን ፍቺ ትርጉም፦ Amharic Translation - Africa Academy፣ እትም 1.0.3፤ ከQuranEnc.com ያለ ምንም ለውጥ የቀረበ። (QuranEnc.com)
ትርጉም የቁርኣንን ፍቺዎች ያስተላልፋል እንጂ ራሱ ቁርኣን አይደለም፤ ቁርኣን ከላይ ያለው የዐረብኛ ጽሑፍ ነው።