የተርቲል አርማተርቲልቀጥታ ሬዲዮ

ሱራ አል ኢንፊጣር፦ ጽሑፉ እና የቁርኣን ፍቺ ትርጉሙ

በሙስሐፉ ውስጥ 82ኛው ሱራ ነው፤ 19 አንቀጾች አሉት፤ በገጽ 587 ይጀምራል።

ቲላዋዎቹን አዳምጥይህን ሱራ በሙስሐፉ ከተፍሲር ጋር አንብብ‹ ሱራ አት ተክዊርሱራ አል ሙጠፊፊን ›

بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

1. ሰማይ በተሰነጠቀች ጊዜ፤

2. ከዋክብትም ተበታትነው በወደቁ ጊዜ፤

3. ባህሮችም በተከፈቱና በተደባለቁ ጊዜ፤

4. መቃብሮችም በተገለባበጡና ሙታን በተነሱ ጊዜ፤

5. (ያኔ) ማንኛይቱም ነፍስ ያስቀደመችውንና ያዘገየችውን ታውቃለች።

6. አንተ ሰው ሆይ! በቸሩ ጌታህ ምን አታለለህ?

7. በዚያ በፈጠረህ፤ አካለ ሙሉም ባደረገህ፤ ባስተካከለህም፤

8. በማንኛውም (እርሱ) በፈለገው ቅርጽ በገጣጠመህ ጌታህ ምን አታለለህ?

9. (ሰዎች ሆይ!) ተከልከሉ፤ ይልቁንም በፍርዱ ቀን ታስተባብላላችሁ።

10. በእናንተ ላይ ጠባቂዎች ያሉባችሁ ስትሆኑ፤

11. የተከበሩ ጸሐፊዎች የሆኑ (ተጠባባቂዎች)፤

12. የምትሰሩትን (ሁሉ) ያውቃሉ፤

13. (እውነተኞቹ) ደጋጎች በእርግጥም በገነት ውስጥ ናቸው።

14. ከሓዲያንም በእርግጥ በገሀነም ውስጥ ናቸው።

15. በፍርዱ ቀን ይገቧታል።

16. እነርሱም (ምን ጊዜም) ከእርሷ ራቂዎች አይደሉም።

17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የፍርዱ ቀን ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?

18. ከዚያም የፍርዱ ቀን ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?

19. (እርሱ) ማንኛይቱም ነፍስ ለሌላይቱ ነፍስ ምንም ማድረግ የማትችልበት ቀን ነው። ነገሩም ሁሉ በዚያ ቀን ለአላህ ብቻ ነው።

የቁርኣን ፍቺ ትርጉም፦ Amharic Translation - Africa Academy፣ እትም 1.0.3፤ ከQuranEnc.com ያለ ምንም ለውጥ የቀረበ። (QuranEnc.com)

ትርጉም የቁርኣንን ፍቺዎች ያስተላልፋል እንጂ ራሱ ቁርኣን አይደለም፤ ቁርኣን ከላይ ያለው የዐረብኛ ጽሑፍ ነው።

ቲላዋዎቹን አዳምጥይህን ሱራ በሙስሐፉ ከተፍሲር ጋር አንብብ‹ ሱራ አት ተክዊርሱራ አል ሙጠፊፊን ›