በሙስሐፉ ውስጥ 86ኛው ሱራ ነው፤ 17 አንቀጾች አሉት፤ በገጽ 591 ይጀምራል።
بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
1. በሰማዩ እና ሌሊት በሚመጣውም እምላለሁ።
2. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሌሊት መጪው ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?
3. ጨለማውን ሰንጣቂ ኮከብ ነው።
4. ነፍስ ሁሉ በእርሷ ላይ ጠባቂ ያለባት እንጂ ሌላ አይደለችም።
5. የሰው ልጅ ከምን እንደተፈጠረ ይመልከት፤
6. ከተስፈንጣሪ ውሃ (የዘር ፈሳሽ) ተፈጠረ።
7. ከጀርባና ከእርግብግቢቶች መካከል የሚወጣ ከሆነ የዘር ፈሳሽ ውሃ (ተፈጠረ)።
8. አላህ እርሱን በመመለሱ ላይ በእርግጥ ቻይ ነው።
9. ሚስጥሮች በሚገለጹበት ቀን፤
10. (ለሰው) ምንም ኃይልና ረዳት አይኖረዉም።
11. የመመለስ ባለቤት (ዝናባማ) በሆነችው ሰማይ እምላለሁ።
12. (በበቃይ) የመሰንጠቅ ባለቤት በሆነችው ምድርም እምላለሁ።
13. እርሱ (ቁርኣን)፤ (እውነትን ከውሸት) የሚለይ (የአላህ) ቃል ነው።
14. እርሱም ቀልድ አይደለም።
15. እነርሱ በእርግጥ ተንኮልን ያሴራሉ (ይሸርባሉ)።
16. እኔም (ለእነርሱ) ዘዴን እዶልታለሁ (አዘጋጃለሁ)።
17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሓዲያንን ቀን ስጣቸው። ጥቂትን ጊዜ አቆያቸው (ታገሳቸው)።
የቁርኣን ፍቺ ትርጉም፦ Amharic Translation - Africa Academy፣ እትም 1.0.3፤ ከQuranEnc.com ያለ ምንም ለውጥ የቀረበ። (QuranEnc.com)
ትርጉም የቁርኣንን ፍቺዎች ያስተላልፋል እንጂ ራሱ ቁርኣን አይደለም፤ ቁርኣን ከላይ ያለው የዐረብኛ ጽሑፍ ነው።