በሙስሐፉ ውስጥ 87ኛው ሱራ ነው፤ 19 አንቀጾች አሉት፤ በገጽ 591 ይጀምራል።
بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የዚያን ከሁሉ በላይ የሆነውን ጌታህን ስም አጥራ (አሞግስ)።
2. ያ ሁሉን ነገር የፈጠረውንና ያስተካከለውን፤
3. ያን የወሰነውን ነገርንም ሁሉ ለተፈጠረለት የመራውን፤
4. ያም ግጦሽን ለምለም አድርጎ ያወጣውን፤
5. (ከዚያ) ደረቅ ጥቁር ያደረገውንም (አምላክ ስም አሞግስ)።
6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቁርኣንን በእርግጥ እናስነብብሃለን፤ አትረሳምም፤
7. አላህ ከፈለገው ነገር በስተቀር፤ እናም እርሱ ግልጹንም የሚሸሽገውንም ሁሉ ያውቃልና፤
8. ለገሪቱም (ሕይወት እስላምን ትከተል ዘንድ) እናገራሃለን።
9. (ሰዎችንም) ገስፅ፤ ግሳፄይቱ ብትጠቅም።
10. (አላህን) የሚፈራ በእርግጥ ይገሰፃል።
11. መናጢዉም ይርቃታል።
12. ያ! ታላቂቱን እሳት የሚገባው፤
13. ከዚያም በእርሷ ውስጥ የማይሞትና ህያዉም የማይሆነው።
14. (አላህን ከማመፅ) የተጥራራ ሰው በእርግጥ ዳነ፤
15. የጌታውንም ስም ያወሳና የሰገደ።
16. ይልቁንም ቅርቢቱን ሕይወት ታስቀድማላችሁ፤
17. (ሰዎች ሆይ!) መጨረሻይቱ ሕይወት በላጭና፤ ዘወታሪ ሆና ሳለ።
18. ይህ በቀደምቶቹም መጻሕፍት ውስጥ ያለ ነው።
19. በኢብራሂምና በሙሳ መጽሐፍት ውስጥ የሰፈረ እውነታ ነው።
የቁርኣን ፍቺ ትርጉም፦ Amharic Translation - Africa Academy፣ እትም 1.0.3፤ ከQuranEnc.com ያለ ምንም ለውጥ የቀረበ። (QuranEnc.com)
ትርጉም የቁርኣንን ፍቺዎች ያስተላልፋል እንጂ ራሱ ቁርኣን አይደለም፤ ቁርኣን ከላይ ያለው የዐረብኛ ጽሑፍ ነው።