የተርቲል አርማተርቲልቀጥታ ሬዲዮ

ሱራ አል ዐለቅ፦ ጽሑፉ እና የቁርኣን ፍቺ ትርጉሙ

በሙስሐፉ ውስጥ 96ኛው ሱራ ነው፤ 19 አንቀጾች አሉት፤ በገጽ 597 ይጀምራል።

ቲላዋዎቹን አዳምጥይህን ሱራ በሙስሐፉ ከተፍሲር ጋር አንብብ‹ ሱራ አት ቲንሱራ አል ቀድር ›

بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በዚያ (ሁሉንም ነገር) በፈጠረ ጌታህ ስም (ጀምርና) አንብብ! [1]

[1] ይህ አንቀጽና ቀጥሎ ያሉት ከቁርአን መጀመሪያ የወረዱ አንቀጾች ናቸው። በኑር ተራራ ላይ በምገኘው የሂራእ ዋሻ ውስጥ ነቢዩ ሰ/ዐ/ወ/ ኸልዋ ወጥተው እያሉ ነው የወረደባቸው። (ቡኻሪና ሙስሊም፤ የወህይ አጀማመር ምእራፍ)

2. ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)።

3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንብብ! ጌታህም በጣም ቸር ነው።

4. ያ በብዕር ያስተማረ (ጌታ)፤

5. የሰውን ልጅ ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ (ጌታ)።

6. በእውነቱ የሰው ልጅ ወሰንን ያልፋል።

7. ራሱን የተብቃቃ ሆኖ በማየቱ ምክንያት

8. መመለሻው ወደ ጌታህ ብቻ ነው።

9. ያንን የሚከለክለውን አየህን?

10. ባሪያን በሰገደ ጊዜ (የሚከለክለውን):

11. እስቲ ንገረኝ (ተከልካዩ ባሪያየ) በትክክል መንገድ ላይ ቢሆን፤

12. ወይም (ፈጣሪውን) በመፍራት ቢያዝ ምን እንደሚሆን አየህን?

13. እስቲ ንገረኝ (ከልካዩ) ቢያስተባብልና ከእምነት ቢሸሽ፤

14. አላህ የሚያይ መሆኑን አያውቅምን?

15. ይታቀብ፤ የማይከለከል ከሆነ በእርግጥ አናቱን ይዘን እንጎትተዋለን።

16. ያቺን ውሸታምና ስህተተኛ የሆነችውን አናቱን።

17. ሸንጎውንም ይጥራ፤

18. እኛም ዘበኞቻችንን እንጠራለን።

19. በጭራሽ፤ (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህን ለሚል ከሓዲ አትታዘዘው፤ ስገድ፤ ወደ አላህም ተቃረብ። [1]

[1] እዚህ የንባብ ሱጁድ አለ። ይህ የመጨረሻ ሱጁድ ነው።

የቁርኣን ፍቺ ትርጉም፦ Amharic Translation - Africa Academy፣ እትም 1.0.3፤ ከQuranEnc.com ያለ ምንም ለውጥ የቀረበ። (QuranEnc.com)

ትርጉም የቁርኣንን ፍቺዎች ያስተላልፋል እንጂ ራሱ ቁርኣን አይደለም፤ ቁርኣን ከላይ ያለው የዐረብኛ ጽሑፍ ነው።

ቲላዋዎቹን አዳምጥይህን ሱራ በሙስሐፉ ከተፍሲር ጋር አንብብ‹ ሱራ አት ቲንሱራ አል ቀድር ›