በሙስሐፉ ውስጥ 97ኛው ሱራ ነው፤ 5 አንቀጾች አሉት፤ በገጽ 598 ይጀምራል።
بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
1. እኛ (ቁርኣንን) በመወሰኛይቱ ሌሊት ውስጥ አወረድነው።
2. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የመወሰኛይቱ ሌሊት ምን እንደሆነች ምን አሳወቀህ?
3. የመወሰኛይቱ ሌሊት ከሺህ ወር የምትበልጥ ነች።
4. በእርሷ ውስጥ መላዕክትና ሩሕም (ጂብሪል) በጌታቸው ፈቃድ በሁሉም ጉዳዮች ይዘው ይወርዳሉ።
5. እርሷም ጎህ እስኪወጣ ድረስ ሰላም ነች።
የቁርኣን ፍቺ ትርጉም፦ Amharic Translation - Africa Academy፣ እትም 1.0.3፤ ከQuranEnc.com ያለ ምንም ለውጥ የቀረበ። (QuranEnc.com)
ትርጉም የቁርኣንን ፍቺዎች ያስተላልፋል እንጂ ራሱ ቁርኣን አይደለም፤ ቁርኣን ከላይ ያለው የዐረብኛ ጽሑፍ ነው።