የተርቲል አርማተርቲልቀጥታ ሬዲዮ

ሱራ አል ሁመዛህ፦ ጽሑፉ እና የቁርኣን ፍቺ ትርጉሙ

በሙስሐፉ ውስጥ 104ኛው ሱራ ነው፤ 9 አንቀጾች አሉት፤ በገጽ 601 ይጀምራል።

ቲላዋዎቹን አዳምጥይህን ሱራ በሙስሐፉ ከተፍሲር ጋር አንብብ‹ ሱራ አል ዓስርሱራ አል ፊል ›

بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

1. ለሐሜተኛ፤ ለዘላፊ፤ (ለአሽሟጣጭ ሁሉ) ወዮለት።

2. ለዚያ ገንዘብን የሰበሰበና የቆጣጠረው (ያደለበዉም) ለሆነ ሁሉ ወዮለት።

3. ገንዘቡ በዚህች ዓለም ዘውታሪ እንደሚያደርገው ያስባል።

4. በጭራሽ፤ አውዳሚና የምትፈጭ በሆነችው እሳት ውስጥ በእርግጥ ይጣላል።

5. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የምትፈጨዋም ምን እንደሆነች ምን አሳወቀህ?

6. የተቀጣጠለችው የአላህ እሳት ናት።

7. ያቺ በልቦች ላይ እንኳን ሳይቀር የምትዘልቅ የሆነች።

8. እርሷ በእርግጥ በእነርሱ ላይ የተዘጋች ናት።

9. በተዘረጋች አዕማድ ውስጥ የተዘጋች ናት።

የቁርኣን ፍቺ ትርጉም፦ Amharic Translation - Africa Academy፣ እትም 1.0.3፤ ከQuranEnc.com ያለ ምንም ለውጥ የቀረበ። (QuranEnc.com)

ትርጉም የቁርኣንን ፍቺዎች ያስተላልፋል እንጂ ራሱ ቁርኣን አይደለም፤ ቁርኣን ከላይ ያለው የዐረብኛ ጽሑፍ ነው።

ቲላዋዎቹን አዳምጥይህን ሱራ በሙስሐፉ ከተፍሲር ጋር አንብብ‹ ሱራ አል ዓስርሱራ አል ፊል ›