በሙስሐፉ ውስጥ 113ኛው ሱራ ነው፤ 5 አንቀጾች አሉት፤ በገጽ 604 ይጀምራል።
بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! እንዲህ) በል፡ -በተፈልቃቂው ጎህ (በአል-ፈለቅ) ጌታ እጠበቃለሁ፤-
2. ከፈጠረው ፍጡር ሁሉ ክፋት።
3. ከሌሊትም ክፋት በጨለመ ጊዜ፤
4. በቋጠሮዎች ላይ ተፊዎች ከሆኑት ደጋሚ ሴቶችም ክፋት፤
5. ከምቀኛም ክፋት፤ በተመቀኘ ጊዜ (በአሏህ) -እጠበቃለሁ- በል።
የቁርኣን ፍቺ ትርጉም፦ Amharic Translation - Africa Academy፣ እትም 1.0.3፤ ከQuranEnc.com ያለ ምንም ለውጥ የቀረበ። (QuranEnc.com)
ትርጉም የቁርኣንን ፍቺዎች ያስተላልፋል እንጂ ራሱ ቁርኣን አይደለም፤ ቁርኣን ከላይ ያለው የዐረብኛ ጽሑፍ ነው።