የተርቲል አርማተርቲልቀጥታ ሬዲዮ

ሱራ አል ዓዲያት፦ ጽሑፉ እና የቁርኣን ፍቺ ትርጉሙ

በሙስሐፉ ውስጥ 100ኛው ሱራ ነው፤ 11 አንቀጾች አሉት፤ በገጽ 599 ይጀምራል።

ቲላዋዎቹን አዳምጥይህን ሱራ በሙስሐፉ ከተፍሲር ጋር አንብብ‹ ሱራ አል ዘልዘላህሱራ አል ቃሪዓሕ ›

بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

1. እያለከለኩ ሩዋጮች በሆኑ (ፈረሶች)፤

2. ምድርን በሸሆናቸው እያጋጩ የእሳት ብልጭታን አውጪዎች በሆኑትም (ፈረሶች)፤

3. በማለዳ (በጧት) ወራሪዎች በሆኑትም ፈረሶች፤

4. በእርሱም አቧራን በቀሰቀሱት፤

5. በፈረሰኞቻቸው በኩል (የጠላት) ስብስብ መሀልን በተጋፈጡትም (ፈረሶች) እምላለሁ።

6. የሰው ልጅ ለጌታው (ጸጋ) በጣም ውለታ ቢስ ነው።

7. እርሱም በዚያ (ክህደቱ) ላይ መስካሪ ነው።

8. እርሱም ገንዘብን በመውደድ ላይ በጣም ብርቱ ነው።

9. የሰው ልጅ በመቃብሮች ዉስጥ ያሉት ሙታን ሁሉ በተቀሰቀሱ ጊዜ ምን እንደሚከሰት አያውቅምን?

10. በልቦች ውስጥ ያለዉም ሁሉ በተገለጸ ጊዜ እንዴት እንደሚሆን አያውቅምን?

11. ጌታቸው በዚያ ቀን በእነርሱ ነገር በእርግጥ ውስጠ አዋቂ ነው።

የቁርኣን ፍቺ ትርጉም፦ Amharic Translation - Africa Academy፣ እትም 1.0.3፤ ከQuranEnc.com ያለ ምንም ለውጥ የቀረበ። (QuranEnc.com)

ትርጉም የቁርኣንን ፍቺዎች ያስተላልፋል እንጂ ራሱ ቁርኣን አይደለም፤ ቁርኣን ከላይ ያለው የዐረብኛ ጽሑፍ ነው።

ቲላዋዎቹን አዳምጥይህን ሱራ በሙስሐፉ ከተፍሲር ጋር አንብብ‹ ሱራ አል ዘልዘላህሱራ አል ቃሪዓሕ ›