የተርቲል አርማተርቲልቀጥታ ሬዲዮ

ሱራ አል ቃሪዓሕ፦ ጽሑፉ እና የቁርኣን ፍቺ ትርጉሙ

በሙስሐፉ ውስጥ 101ኛው ሱራ ነው፤ 11 አንቀጾች አሉት፤ በገጽ 600 ይጀምራል።

ቲላዋዎቹን አዳምጥይህን ሱራ በሙስሐፉ ከተፍሲር ጋር አንብብ‹ ሱራ አል ዓዲያትሱራ አት ተካሱር ›

بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

1. ቆርቋሪይቱ (ጩኸት)፤

2. ቆርቋሪይቱ (ጩኸት) ምንድን ናት!

3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቆርቋሪይቱ ምን እንደሆነች ምን አሳወቀህ?

4. ሰዎች እንደተበታተነ ቢራቢሮ (ኩብኩባ) የሚሆኑበት ቀን፤

5. ጋራዎችም እንደ ተነደፈ ሱፍ የሚሆኑበት (አስደንጋጭ ቀን) ናት።

6. (በዚያ ዕለት) ያ ሚዛኖቹ የከበዱለት ሰውማ

7. እርሱ በአስደሳች ኑሮ (በገነት) ውስጥ ይሆናል።

8. ያ ሚዛኖቹ የቀለሉበት ሰው ደግሞ

9. መኖሪያው ሃዊያህ (የምትባል የገሀነም እሳት) ናት።

10. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እርሷ ምን እንደሆነች ምን አሳወቀህ?

11. (እርሷ) በጣም ተኳሳ እሳት ናት።

የቁርኣን ፍቺ ትርጉም፦ Amharic Translation - Africa Academy፣ እትም 1.0.3፤ ከQuranEnc.com ያለ ምንም ለውጥ የቀረበ። (QuranEnc.com)

ትርጉም የቁርኣንን ፍቺዎች ያስተላልፋል እንጂ ራሱ ቁርኣን አይደለም፤ ቁርኣን ከላይ ያለው የዐረብኛ ጽሑፍ ነው።

ቲላዋዎቹን አዳምጥይህን ሱራ በሙስሐፉ ከተፍሲር ጋር አንብብ‹ ሱራ አል ዓዲያትሱራ አት ተካሱር ›