በሙስሐፉ ውስጥ 110ኛው ሱራ ነው፤ 3 አንቀጾች አሉት፤ በገጽ 603 ይጀምራል።
بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የአላህ እርዳታና (የመካ) መከፈት በመጣ ጊዜ፤
2. ሰዎችም ቡድን ቡድን እየሆኑ ወደ አላህ ሃይማኖት ሲገቡ ባየህ ጊዜ፤
3. ጌታህን ከማመስገን ጋር አጥራው። ምህረትንም ለምነው፤ እርሱ ጸጸትን በጣም ተቀባይ ነውና።
የቁርኣን ፍቺ ትርጉም፦ Amharic Translation - Africa Academy፣ እትም 1.0.3፤ ከQuranEnc.com ያለ ምንም ለውጥ የቀረበ። (QuranEnc.com)
ትርጉም የቁርኣንን ፍቺዎች ያስተላልፋል እንጂ ራሱ ቁርኣን አይደለም፤ ቁርኣን ከላይ ያለው የዐረብኛ ጽሑፍ ነው።