የተርቲል አርማተርቲልቀጥታ ሬዲዮ

ሱራ አል ካፊሩን፦ ጽሑፉ እና የቁርኣን ፍቺ ትርጉሙ

በሙስሐፉ ውስጥ 109ኛው ሱራ ነው፤ 6 አንቀጾች አሉት፤ በገጽ 603 ይጀምራል።

ቲላዋዎቹን አዳምጥይህን ሱራ በሙስሐፉ ከተፍሲር ጋር አንብብ‹ ሱራ አል ከውሰርሱራ አን ነስር ›

بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!)- (ለከሓዲያን እንዲህ) በላቸው፡- እናንተ ከሓዲያን ሆይ!

2. ያንን የምትገዙትን (ጣዖት አሁን) አልገዛም።

3. እናንተም እኔ የምገዛውን (አምላክ አሁን) ተገዢዎች አይደላችሁም።

4. እኔም ያንን የተገዛችሁትን (ወደ ፊት) ተገዢ አይደለሁም።

5. እናንተም እኔ የምገዛውን (ወደ ፊት) ተገዢዎች አይደላችሁም።

6. እናንተ የራሳችሁ ሃይማኖት አላችሁ። እኔም የራሴ ሃይማኖት አለኝ -በላቸው።

የቁርኣን ፍቺ ትርጉም፦ Amharic Translation - Africa Academy፣ እትም 1.0.3፤ ከQuranEnc.com ያለ ምንም ለውጥ የቀረበ። (QuranEnc.com)

ትርጉም የቁርኣንን ፍቺዎች ያስተላልፋል እንጂ ራሱ ቁርኣን አይደለም፤ ቁርኣን ከላይ ያለው የዐረብኛ ጽሑፍ ነው።

ቲላዋዎቹን አዳምጥይህን ሱራ በሙስሐፉ ከተፍሲር ጋር አንብብ‹ ሱራ አል ከውሰርሱራ አን ነስር ›