በሙስሐፉ ውስጥ 93ኛው ሱራ ነው፤ 11 አንቀጾች አሉት፤ በገጽ 596 ይጀምራል።
بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
1. በረፋዱም፤ (እምላለሁ)
2. በሌሊትም ጸጥ ባለ ጊዜ እምላለሁ።
3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ አላሰናበተህም፤ አልጠላህምም።
4. የመጨረሻይቱ ዓለም ከመጀመሪያይቱም ይልቅ ላንተ በላጭ ናት።
5. ጌታህም ወደ ፊት (ብዙ ስጦታ) በእርግጥ ይሰጥሃል። ትደሰታለህም።
6. የቲም ሆነህ አላገኘህምና አላስጠጋህምን? (አስጠግቶሃል)።
7. (የሸሪዓን ሕግጋት) የማታውቅ ሆነህ አገኘህና መራህ።
8. ደሃም ሆነህ አገኘህና አበለጸገህ።
9. እናም የቲምን አትጨቁን።
10. ለማኝንም አትገላምጥ።
11. የጌታህንም ጸጋ ግለጽ።
የቁርኣን ፍቺ ትርጉም፦ Amharic Translation - Africa Academy፣ እትም 1.0.3፤ ከQuranEnc.com ያለ ምንም ለውጥ የቀረበ። (QuranEnc.com)
ትርጉም የቁርኣንን ፍቺዎች ያስተላልፋል እንጂ ራሱ ቁርኣን አይደለም፤ ቁርኣን ከላይ ያለው የዐረብኛ ጽሑፍ ነው።