በሙስሐፉ ውስጥ 94ኛው ሱራ ነው፤ 8 አንቀጾች አሉት፤ በገጽ 596 ይጀምራል።
بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልብህን ላንተ አላሰፋንልህም?
2. ሸክምህንም አላወረድንልህምን?
3. ያንን ጀርባህን ያከበደውን (ሸክም)
4. መወሳትህንም ከፍ አላደረግንልህ?
5. እናም ከችግር ጋር በእርግጥ ምቾት አለ።
6. ከችግር ጋር በእርግጥ ምቾት አለ።
7. (የጀመርከውን ጥሩ ስራ) በጨረስክ ጊዜ ወደ ሌላ ጥሩ ስራ ቀጥል (አስከትል)።
8. ክጃሎትህንም ወደ ጌታህ ብቻ አድርግ።
የቁርኣን ፍቺ ትርጉም፦ Amharic Translation - Africa Academy፣ እትም 1.0.3፤ ከQuranEnc.com ያለ ምንም ለውጥ የቀረበ። (QuranEnc.com)
ትርጉም የቁርኣንን ፍቺዎች ያስተላልፋል እንጂ ራሱ ቁርኣን አይደለም፤ ቁርኣን ከላይ ያለው የዐረብኛ ጽሑፍ ነው።